ቅዱሳን መላእክት
መላእክት የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ክፍል እና ምዕራፍ ተጽፎ
እናገኛለን፡፡ ነገር ግን በእነዚህ የተጠቀሱት ክፍሎች ውስጥ የተጠቀሱት ሁሉ ቅዱሳን መላእክትን ይመለከታሉ ማለት
ግን አይደለም፡፡ መላእክት የሚለውን ስም መጽሐፍ ቅዱስ እንደየ አገባቡ ለሦስት ነገሮች ሲጠቀምበት እንመለከታለን፡፡
ሀ. አለቆች፣ገዢዎች ሲል
መልአክ የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን <ገዢ፣አስተዳዳሪ፣አለቃ›
የሚል ፍቺን ይሰጣል፡፡ይኸውም በዮሐ 3፥1 ላይ ምስጢረ ጥምቀትን እንደሚገባ አድርጎ ስላስተማረው ስለ አይሁድ
አለቃ ኒቆዲሞስ ሲናገር በግዕዙ ‹ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እም ፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ መልአኮሙ ለአይሁድ› በማለት
ሲገልጸው የአማርኛ አቻ ትርጉሙም ‹ከፈሪሳውያን ወገን የሚሆን ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል የአይሁድ አለቃ› የሚል
ነው፡፡
ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ መላእክት ተብሎ መጠቀሱ ገዢን አለቅነትን ለማመልከት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተጨማሪም ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቶስን በማመናቸው እና በመከተላቸው እርሱና ሐዋርያቱ ለሰዎች እንዲሁም ለሹማምንት መጫወቻ እና መዘባበቻ እንደሆኑ ሲናገር ‹ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ ሆነናልና› በማለት ገልጾታል፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋልና ማጤን ያለብን ነገር ቢኖር መላእክት ብሎ የጠቀሰው የምድር ሹማምንትን እንጂ ፌዝ እና ስላቅ የሌለባቸው ንጹሐን መላእክትን እንዳልሆነ ነው፡፡ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂዎችንና አስተዳዳሪዎችን መላእክት በማለት ጠርቷቸዋል፡፡ (1 ቆሮ 4፥9 ፣ራእይ 1፥20)
ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ መላእክት ተብሎ መጠቀሱ ገዢን አለቅነትን ለማመልከት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተጨማሪም ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቶስን በማመናቸው እና በመከተላቸው እርሱና ሐዋርያቱ ለሰዎች እንዲሁም ለሹማምንት መጫወቻ እና መዘባበቻ እንደሆኑ ሲናገር ‹ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ ሆነናልና› በማለት ገልጾታል፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋልና ማጤን ያለብን ነገር ቢኖር መላእክት ብሎ የጠቀሰው የምድር ሹማምንትን እንጂ ፌዝ እና ስላቅ የሌለባቸው ንጹሐን መላእክትን እንዳልሆነ ነው፡፡ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂዎችንና አስተዳዳሪዎችን መላእክት በማለት ጠርቷቸዋል፡፡ (1 ቆሮ 4፥9 ፣ራእይ 1፥20)
ለ. ሠራዊተ አጋንንትን
ተፈጥሮአቸው እንደ መላእክት የሆነ ኋላ ግን በገዛ ፈቃዳቸው
ከእግዚአብሔር ከአምላካቸው የተነጠሉ ከመንግስቱ የተለዩ ሠራዊተ አጋንንትን መጽሐፍ ቅዱስ መላእክት በማለት
ይጠራቸዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ዓላማቸውን ስለሳቱትና ክብራቸውን ስለተነፈጉት ሠራዊተ አጋንንት እስከ ምፅአተ
ክርስቶስ ድረስ ከጨለማ በታች ሆነው በእስራት እንደሚቆዩ ሲናገር ‹መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን
አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም
እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል› ብሏል፡፡ኢዮብም አምላክነትን ሽቶ ፈጣሪውን ክዶ
በተዋረደና በስንፍና መረብ በተጠላለፈ ሰይጣንና ሠራዊቱ እግዚአብሔር እንደ ማይተማመን ሲገልጽ ‹እነሆ፥ በባሪያዎቹ
አይታመንም መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል› ነገር ግን ይህቺን ጥቅስ በመያዝ ትጉሃን የሆኑ የእግዚአብሔርን
አገልጋዮች ቅዱሳን መላእክትን ለመንቀፍ የሚጣጣሩ መናፍቃን አሉ፡፡ ‹እግዚአብሔር ያከበረውን ማን ያቀለዋል!› ምንም
የስም አጠራራቸውን ሊያጠፉ ቢጥሩም ከምንም በላይ ግን ቅዱሳን መላእክት ስማቸው በእግዚአብሔር ፊት የሰለጠነ ነው!፡፡ (ያዕ 1፥6 ፣ ኢዮ 4፥18)
ሐ. ቅዱሳን መላእክት
መላእክት የሚለው ቃል በሌላ አገባብ ‹ለአከ› ከሚለው የግዕዝ ግስ
የወጣ ሲሆን መልእክተኛ ፣ ተላላኪ የሚል ትርጉም ይሰጠናል፡፡ ይህንንም የአገባብ ትርጉም የምንጠቀመው ለቅዱሳን
መላእክት ብቻ ሲሆን ነው፡፡ ይህንን ትርጉም በመጠቀም በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ቅዱሳን መላእክትን
ተጠቅሰው እናያለን፡፡ ለአብነት ያህልም አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ተኝቶ ባያት ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ
መሰላል ላይ ሲወጡና ሲወርዱ የነበሩትን መላእክት ከላይ ከጠቀስናቸው የአገባብ ትርጉሞች ውጪ መሆኑን ሲያመለክተን ‹የእግዚአብሔር መላእክት› በማለት ጠርቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› በማለት ከሠራዊተ አጋንንት እና ለገዢዎች ከሚሰጠው ትርጉም በተለየ መልኩ ከትቦታል፡፡(ዘፍ.28፥12፣ ዘፍ. 32፥1፣ መዝ 33፥7፣ዕብ 1፥6)
በአጠቃላይ ‹መላእክት› የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ሦስት አይነት
የአገባብ ፍቺ እንዳለው ካወቅን ይህ ጽሑፋችንም የሚያተኩረው በቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮ እና አገልግሎት ላይ
ይሆናል፡፡ ቅዱሳን መላእክት የተፈጠሩት በእለተ እሁድ ሲሆን ስለተፈጥሯቸውም በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ዘንድ ሁለት
አይነት ሐሳብ አለ፡፡
የመጀመሪያው ሐሳብ ከእሳትና ከነፋስ ተፈጥረዋል የሚል ሲሆን እንደ
ማስረጃነትም የሚያቀርቡት በመጽሐፈ መቃብያን የተጠቀሰውን ‹‹ ወሶበ ኢያዕኮትኮ ለዘፈጠረከ እምነፋስ ወነድ ›› ‹‹
ረቂቅ የምትሆን አንተ ከእሳትና ከነፋስ የፈጠረህን አላመሰግንም ባልክ ጊዜ…›› የሚለውን እና በዳዊት መዝሙር ላይ
የተጠቀሰውን ‹ዘይሬስዮሙ ለመላእክቲሁ መንፈሰ ወለእለ ይትለአክዎ ነደ እሳት›› ‹‹ መላእክቱን መንፈስ
አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ ›› የሚሉት ይካተቱበታል፡፡ መዝ. 103፥4፡፡
ሁለተኛው ደግሞ ከእሳትና ከነፋስ አልተፈጠሩም የሚሉት ሲሆኑ እነዚህም
የሚያቀርቡት ማስረጃ ‹‹ሶበሰ ተፈጥሩ እምነፋስ ወነድ እሞቱ ወእማሰኑ ከማነ›› ‹እነሱስ ከእሳትና ከነፋስ
ተፈጥረው ቢሆን እንደኛ ታማሚ ሟች በሆኑ ነበር›› የሚለውን በመጽሐፈ አክሲማሮስ ላይ የተጠቀሰውን በመመርኮዝ
ነው፡፡ ሁለቱን ሲያስታርቁት ግን ከእሳትና ከነፋስ ተፈጠሩ ማለቱ በግብር (በስራ) ስለሚመስሉት ነው፡፡ ይኸውም
እሳት ረቂቅ እንደሆነ መላእክትም ረቂቃን ናቸው፤ እሳት ኃያል ነው መላእክትም ኃያላን ናቸው፤ እሳት ብሩህ እንደሆነ
መላእክትም ብሩሃነ አእምሮ መሆናቸውን ሲያመለክት፤ ከነፋስ ተፈጠሩ ማለቱም ነፋስ ፈጣን እንደሆነ እነርሱም
ለተልእኮ ፈጣን መሆናቸውን ለማመልከት እንጂ ተፈጥሯቸውስ ‹‹እምኀበ አልቦ ኀበቦ›› ‹‹እምኀበ ኢምንት ኀበ
ምንት›› ካለመኖር ወደ መኖር ነው፡፡
የኢትዮጽያ ቤተ ክርስቲያን ለነገረ ቅዱሳን ካላት ታላቅ አክብሮትና
ፍቅር የተነሳ እንኳን ሥራቸውንና ትምህርታቸውን ቀርቶ ስማቸውንም በፊደል ለይታ ልዩ በሆነ ምስጢርና አንድምታዊ
ትርጉም አሰባጥራ ለልጆቿ ለምእመናን ታስተምራለች፡፡እኛም ይህን አብነት በማድረግ በዚች ጽሑፍ የመላእክትን ክብርና
አገልግሎት ከስማቸው ፊደል ፍቺ ጋር አዋህደን ለማየት እንሞክራለን፡፡
መጋብያን
ከመላእክት አገልግሎትና ተልእኮ መካከል የሰውን ልጅ ለቁመተ ስጋ
የሚሆን ምግብን መመገብ አንዱ ነው፡፡ይህም ሐሳብ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተከትቦ (ተጽፎ)
እናገኘዋለን፡፡ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ፍቅረ ጣኦት ካናወዛት ከንግስት ኤልዛቤል ጋር ተጣልቶ በተሰደደ ጊዜ ድካም
ተሰምቶት ከጥላ ስር አንቀላፍቶ ሳለ መልአከ እግዚአብርም የኤልያስን መራብና መጠማት ስላወቀ እንጀራን በአገልግል
ውኃን በመንቀል አድርጎ መግቦት ነበር፡፡(መጽ.ነገ. ቀዳ 19፥2-8) ኅዳር አስራ ሁለት ቀን ቤተ ክርስቲያችን
በታላቅ ድምቀት የምታከብረው የቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያ በዓልም የሚያስታውሰን አርባ ዘመን ሙሉ በበረሀ ሲገዙ ለነበሩ
ሕዝበ እስራኤል መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል መናን ከሰማይ እያወረደ እንደመገባቸውና እስከ ስደታቸው ፍጻሜ በመግቦቱ
እንዳልተለያቸው ነው(ዘጸ 16፥35)፡፡ አንድ አንድ ሰዎች ስለ መላእክት መጋቢነት ሲነገር የሚደንቃቸውና ግራ
የሚያጋባቸው አሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱስን ካለመረዳት የተነሳ ነው እንጂ እንኳን ንጹሐን የእግዚአብሔር አገልጋዮች
መላእክት ቀርቶ ህጸጽ ጉድለት የሚገኝባቸው የሰው ልጆችም እንዲህ ያለውን ስራ እንደሰሩ በሰፊው ተጽፎ እናገኛለን
፡፡ መላእክት ከምግበ ስጋ ባሻገር ምግበ ነፍስ የሆነውንም ጽድቅ ይመግቡናል (ያስተምሩናል) ፡፡ ( ራዕይ 18፥10
ዳን 10፥21)
ላዕላውያን
ይህም ማለት መላእክት ሰማያውያን እንደሆኑ የሚያስረዳን ቃል ነው፡፡
መላእክት ሰማያውያን መሆናቸውን ገባሬሆሙ ለመላእክት (የመላእክት ፈጣሪያቸው) የሆነ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ክቡር በሆነ ወንጌሉ ስለ መላእክት በጠቀሰበት ትምህርቱ ‹‹የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ…›› ‹‹እንደ
እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ…›› እና የመሳሰሉትን ተናግሯል፡፡ ላዕላውያን የሚለው ቃል ሰማያውያን ከሚለው
ፍቺው በተጨማሪ በክብር ከፍ ያሉ ልዑላነ ክብር የሚል ፍቺ ይኖረዋል፡፡ይህም ፍቺ በበለጠ ክቡራን ከሚለው ቃል ፍቺ
ጋር ስለሚወራረስ በዚያ ስር ለማየት እንሞክራለን፡፡ (ማቴ. 24፥36 ማቴ. 22፥30)
እቁባነ ምሕረት
የቃሉ ፍቺ በምሕረት የሚጠብቁ የሚል ሲሆን መላእክት ዑቃቤ (ጠባቂ)
በመባል ይታወቃሉ፡፡ ለርዕሳችንም እንደ መግቢያ የተጠቀምነውም ‹‹በመንገድህም ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁት ቦታም
ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰዳለሁ›› የሚለውም ቃል የሚጠቁመን መላእክት ከእግዚአብሔር ዘንድ
የሚላኩ ጠባቂዎቻችን መሆናቸውን ነው፡፡ የመላእክት አገልግሎት ሰውን መጠበቅ ከመከራ ከችግር ማዳን እንደሆነ ቅዱስ
ጻውሎስ ሲናገር ‹‹ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለመርዳት የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን››
በማለት በተረዳ መልኩ አስቀምጦታል(ዕብ 1፥14)፡፡ታዲያ የመላእክትን ጠባቂነት አለማመን ከክህደት አልፎ በመጽሐፍ
ቅዱስ የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ፍጹም መንቀፍ የጻፉትንም ቅዱሳን ውሸታም ማለት እንደሆነ ማን በነገረን!?
ያለ መላእክት ጠባቂነት የሰው ልጅ እንኳን አርባና ሃምሳ ዘመን ቀርቶ ለአንድ ማይክሮ ሰከንድ ያህል መሰንበት
አይችልም፡፡ ምክንያቱም የመላእክቱ ጥበቃ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና! የሚደንቀው ግን እንዲህ እያቃለልናቸውና
እያጣጣልናቸው እኛን በትጋትና በትእግስት መጠበቃቸው ነው፡፡ በእውነት እንዲህ ላለ ትዕግስት አንክሮ ይገባል! እንደዚህም ላለው ጥበቃ ምስጋና ይገባል!
ክቡራን
መላእክት ክቡራን ይባላሉ፡፡በንጽሕናውና በቅድስናው ከመላእክት ክብር
ጋር የሚተካከል ክብር ያለው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ የመላእክትን ክብር ሲናገር ‹‹ከዚህ በኋላ ታላቅ
ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ሲወርድ አየሁ ከክብሩም የተነሳ ምድር በራች›› በማለት ነበር የገለጸው ራዕይ 18፣1
፡፡እንደዚሁም በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስለ መላእክት ክብር በሰፊው ተጽፎ እናገኛለን፡፡ከነዚህም መካከል
በዘጸ 22 ላይ የተጠቀሰው የበለዓምን ታሪክ ብቻ ጠቅሰን ስለ መላእክት ክብር ብዙ መነጋገር እንችላለን ነገር ግን
ጊዜውም ወረቀቱም ስለሚገድበን በአጭሩ እንመለከተዋለን፡፡በለዓም ምንም ዓይነ ልቡናው ቢታወርበትም ፈቃደ እግዚአብሔር
ሆኖ መልአኩ በተገለጸለት ጊዜ ከክብሩ የተነሳ በግንባሩ ተደፍቶ እንደሰገደለት እናመለከታለን፡፡ ስለዚህ መላእክት
ክቡራን ከመሆናቸውም በላይ ለክብራቸው ከጉልበት በርከክ ብሎ በግንባር መሬት ነክቶ እጅ መንሳት እንደሚገባ ከታሪኩ
እንማራለን፡፡ በተጨማሪ መላእክት ክቡራን ናቸው የምንለው በላያቸው ከሚያድርባቸው ከእግዚአብሔር የተነሳ ነው፡፡
አምላካችን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ባወጣቸው ጊዜ ይረዳቸውና ከመከራ ይታደጋቸው ዘንድ ስለ ላከው መልአክ
ሕዝቡን ሲያስጠነቅቅ ‹‹ ስሜ በርሱ ነውና መልአኬን አታስመርሩት ›› በማለት የእርሱ ክብር በእነርሱ ላይ እንዳለ
በተረዳ ነገር ተናግሮናል፡፡ ስለዚህ መላእክትን አለማክበር በእነርሱ የሚከብር እግዚአብሔርን አለማክበር ነው፡፡
ስማቸውን ጠርቶ ላለመማጸን ‹‹እነርሱ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ብቻ የሚላኩ ተላላኪዎች ናቸው›› ማለት
አያዋጣም፡፡ይልቁኑ ‹እግዚአብሔር ያከበረውን› ማቅለል ሰሪውንና አክባሪውን ተሳስተሃል አርም ማለት በመሆኑ
የገሃነምን ፍርድ ሳያመጣ አይቀርም!!!ስለዚህ መላእክትን እግዚአብሔር ባከበራቸው ክብር ማክበር ይገባል፡፡
ትጉሃን
ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ እንደተናገረ መላእክት ሀያ አራት ሠዓት ሙሉ
ያለማቋረጥ ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል (ኢሳ 6)፡፡‹‹እስመ እረፍቶሙ አኮቴቶሙ
እስመ አኮቴቶሙ እረፍቶሙ›› ‹‹እረፍታቸው ምስጋናቸው ምስጋናቸው እረፍታቸው›› እንዲል፡፡ ከዚህ ግብራቸው የተነሳ
ቤተ ክርስቲያን ትጉሃን ብላ ትጠራቸዋለች፡፡ ት የሚለው ቃል ከትጉሃን በተጨማሪ ትሁታን ተብሎ ይፈታል፡፡ ቅዱስ
ሚካኤል ስለ ሙሴ ስጋ ከሰይጣን ጋር በተከራከረ ጊዜ ሰይጣን ባለው የስድብ አፍ ብዙ ጽርፈትን (ስድብን) በተናገረ
ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ግን እግዚአብሔር ይገስጽህ ከማለት ያለፈ ምንም አልተናገረውም ነበር፡፡ ይህንንም ያደረገው ስለ
ስድቡ ሰይጣንን መቅጣት ሳይችል ወይም ስልጣኑ ሳይኖረው ቀርቶ ሳይሆን ስለ ትህትናው ታገሰው እንጂ፡፡(ይሁ 1፣6)
በአጠቃላይ እስከአሁን የጠቀስናቸው ዝርዝር ሐሳቦች ስለ መላእክት ተፈጥሮ፣ስለ አገልግሎታቸው እንዲሁም ስለ ስማቸው ትርጉም መጠነኛ የሆነ የቤተ ክርስቲያን እውቀት እንደጨበጣችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
source:
ዲ. አቤል ካሳሁን
ስለ አማኝ ሕዝብዋ ደግሞ፡ ˝ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።˝ (መዝ 67÷31) በማለት ፍጹም የሃማኖት አገር መሆንዋን ይገልጻል፡፡
እግዚአብሔር ከመጣብን ርኵሰት ይጠብቀን አገራችንን ይባርክልን!!! አሜን፡፡
አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን፡፡ እመአምላክ ከዚህ ጭንቅ ነገር ታውጣን !!! አሜን፡፡
ኢትዮጵያዊ
ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአርባ ጊዜ በላይ እንደተጻፈ ይታወቃል፡፡
ከመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስንነሳ፡ ገነትን ከሚያጠጡት አራቱ
አፍላጋት አንዱ ግዮን የኢትዮጵያ ወንዝ ነው፡፡ (ዘፍ2÷13) ስሟን ከወንዝዋ የጀመረው መጽሐፍ ቅዱሳችን ፡
ሕዝቦችዋ ለእግዚአብሔር የቀረቡ ባህላቸውን እና ሃይማኖታቸውን ጠባቂዎች መሆናቸውን ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡
ለምሳሌ ˝በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?˝ (ኤር 13÷23)
በማለት ኢትዮጵያውያን የማይለወጡ እምነታቸውን የማይሸቅጡና ዘመን ወረተኛ
የማያደርጋቸው ጽኑአን ሕዝቦች መሆናቸውን ሲገልጽ፡ በሌላ ቦታ ደግሞ ፡ ˝የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ
እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?˝ በሚለው የእግዚአብሔር ቃል፣ ሕዝቦችዋን የታላቁ መጽሐፍ አንኳር ባለታሪክ
እና የእግዚአብሔር በኵር ከተባሉት የእስራኤል ሕዝቦች እኩል መሆናቸውን ሲመሰከር እናነባለን (አሞ 9÷7)
ስለ ጀግንነትዋም፡ ˝ኢትዮጵያውያን…. እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች ነበሩአቸው…˝ (2 ነገ 16÷8) ሲል፤ስለ አማኝ ሕዝብዋ ደግሞ፡ ˝ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።˝ (መዝ 67÷31) በማለት ፍጹም የሃማኖት አገር መሆንዋን ይገልጻል፡፡
መጋቢዋና ጠላቶዎችዋን የሚጥልላት እግዚአብሔር ለመሆኑም፣ ˝አንተም
የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።˝ (መዝ፣ 73÷14) በማለት መዝሙረኛው ዳዊት
ሲመሰክርላት እናያለን፡፡
በአጭሩ ኢትዮጵያ አገራችን የሃይማኖት ፣የታሪክ፣ የባህል እና ጀግንነት
ተምሳሌት ስትሆን ከላይ በጠቀስነው መሰረት በሃይማኖት በኩልም ከዓለም ሁሉ በፊት በሦስቱ ህግጋት ጸንታ የኖረች
በታሪክ ደግሞ በቅኝ ግዛት ሳትደፈር ጸንታ የቆየች ብቸኛዋ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነች አገር ናት፡፡
ይህቺ ታሪካዊት አገራችን ተፈርታና ተከብራ የኖረችው ታዲያ ከሌሎች
አገራት የተለየ ተፈጥሮ ያላቸው ሰዎች የሚኖሩባት ሆና አይደለም ፡፡ ያው ሰዎች ናቸው፡፡ የሕዝቦችዋ ጥንካሬና ድል
አድራጊነት መነሻው በግልጽ እግዚአብሔርን መያዛቸው ብቻ ነው፡፡ ˝ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር
ትዘረጋለች።˝ ስለዚህ አትሸነፍም ተሸንፋም አታውቅም፡፡
ነገሥታቶችዋም ይህንን አውቀው በሄዱበት ሁሉ ታቦት ይዘው ይጓዛሉ
፤ድንኳን ተክለው ካህናትን አስከትለው ያስቀድሳሉ፤ ቤተክርስቲያንን ይተክላሉ… ክፉ ነገር ሲመጣ ጾም ጸሎት
እንዲታወጅ ደርጋሉ ከዚያም በዘመቱበትሁሉ ያሸንፋሉ፡፡ ድላቸው እግዚአብሔር ነው፡፡
እግዚአብሔርም ከመረጣቸው እስራኤል ይልቅ ቅርሱ እንዲቀመጥ የፈቀደው በዚህችው በእኛ ምድር በኢትዮጵያ ነው፡፡ ታቦተ ጽዮን ፣ ግማደ መስቀሉ ወ.ዘ.ተ፡፡
ከአፍሪካ በራስዋ ባህልና ቋንቋ የምትኖር በራሷ ፊደል ልጆችዋን አፍ
የምታስፈታ ሀገር፤ ከዕውቀት በፊት አዋቂ ህዝቦች ያላት ከትምህርት በፊት ምሁራን (ከእግዚአብሔር የተማሩ)
የተገኙባት ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡
ሕዝቦችዋ ደግ ከመሆናቸው የተነሳ እንግዳ ተቀባዮች ፤በሃይማኖተኛነታቸው
ደግሞ የክርስቲያን ደሴት የተባለላት የእግዚአብሔር ሀገር ነች ፡፡ ሰዎች የፈለጉትን በማለት ስሟን ለማጉደፍ ቢጥሩም
እንኳ እግዚአብሔር በመረጣቸው አድሮ እንዲታነጹባት የፈቀዳቸው ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት፤ ታላላቅና ታሪካውያን
ገዳማቶችዋ በእግዚአብሔር እጅ ያለች የእግዚአብሔር ሀገር መሆንዋን እየመሰከሩላት ጠላቶችዋን ሲያሳፍሩ ኖረዋል
ወደፊትም ይኖራሉ፡፡
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ በማንነትዋ ጸንታ እኛ ከንቱዎቹ
አስክንረከባት ድረስ የትውልድ ኩራት ሆና ቆይታለች፣ አክሱም እና ላሊበላ የሐይቅ ፣የጣናና የዝዋይ ደሴቶች ገዳማት
የተሸከሙዋቸው እና ለትውልድ ያቆዩዋቸው ቅዱሳት መጻሕፍት እንኳን ላነበባቸው ለዳሰሳቸው ሁሉ ፈውሶች ናቸው፡፡ ወቅት
የማይለውጣቸውና በየዘመናቱ ሁሉ አዲስ የሆኑት የቅዱስ ያሬድ ዜማዎች ፤ የታላቁ ሊቅ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ስራዎች፤ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትምህርቶች ፤ የመናኙ ወንጌላዊ ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት ጸሎትና
ትምህርት የሌሎችም ታላላቅ አባቶች እና ነገሥታት መሪዎች ጸሎትና መንፈሳዊ ህይወት የመጽሐፍ ቅዱስዋን ኢትዮጵያ
እስከ ዛሬ ጠብቀው አቆይተዋታል፡፡ በረከታቸው ይደርብን!
በቤተ ክርስቲያናችን እንደሚተረከው
እመቤታችን ከሄሮድስ ሽሽት ህፃኑ ኢየሱስን (ልጇ ጌታችንን) ይዛ በተሰደደች ጊዜ ኢትዮጵያ ስትደርስ ጌታችን ይህቺን
የቅዱሳን መፈልፈያ የሆነችን ሀገር ˝አስራት ድርጌ ሰጥቼሻለሁ˝ ብሎ አስራት እንደሰጣት ይሰበካል ክብር ይግባው፡፡
ሁላችንም የምናውቀው የካቲት 23 የሚከበረው የአድዋ ድል ንጉሡ አጼ
ምኒሊክ (እምዬ ምኒሊክ) የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት ይዘው በመውጣታቸው የተገኘ መሆኑን በጦርነቱ የተሸነፉት
ጣልያኖች የመሰከሩት እውነት ነው፡፡
በአጠቃላይ የተቀደሰችው ሀገር ኢትዮጵያ ተወክፎተ ነግድን (እንግዳ
መቀበልን)ገንዘብ ያደረገች፤ ሀገረ ምስካይ (መጠጊያ) ሀገረ ቅዱሳን ፤ በርካታ ጀግኖችን እና ስፍር ቁጥር የሌላቸው
ቅዱሳንን የወለደች የክርስቲያኖች ደሴት ናት፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የነበሩ ነገሥታቶችዋም አብዛኞቹ
ለእግዚአብሔር ያደሩ መንፈሳውያን በመሆናቸው የረከሰ ነገር ወደ ምድሪቱ እንዳይገባ እና ሕዝቦችዋ እንዳይበከሉ
ጠብቀዋታል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ የታፈረች የተከበረች እና በእግዚአብሔር ሀገርነትዋ ታውቃ የምትኖር ሀገር ሆናለች፡፡
ዛሬ ከላይ በጣም በጥቂቱ ብቻ ልንዳስስላት የሞከርነው ታሪክ ባለቤት
ኢትዮጰያ እጅግ እስፈሪ አሰቃቂና ከሕዝቦችዋ ሃማኖት ባህልና ታሪክ ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ ነውር እያስተናገደች
ትገኛለች፡፡ ለወትሮው አዲስ አበባ መንገድ ሲዘጋ ከባለሥልጣኖቻችን አንደኛቸው አልፈው ይሆናል ወይም የመሪዎች
ስብሰባ አለ እንግዶች ናቸው የመሳሰሉ ወሬዎች እንሰማ ነበር፡፡ ሰሞኑን የሚሰማው ወሬ ግን ለየት ያለ ነው፡፡
በየቦታው ፖሊስ ቆሞ ፍተሻ ተጠናክሮ ሲታይ ˝ምንድን ነው?˝ ለሚለው ጥያቄ መልሱ ˝ለእንትኖቹ ነው˝ የሚል ነው፡፡
˝እንትኖቹ˝ እንትን እንድንሆን ሊያበረታቱን የመጡብን እንትኖች!
በአጭሩ በሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረ ሰዶም ስብሰባ
እየተካሄደባት ነው ተባልን፡፡ ወደ እግዚአብሔር እጆችዋን ትዘረጋለች ተብሎ የተመሰከረላት ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ
ከተፈጥሮ ህግ ውጪ የእግዚአብሔርን ስራ የሚፃረር ተግባርን ለማስፋፋት በርዋን ከፍታ ሕዝቦችዋ የማያውቁትን ኃጢአት
ለማለማመድ ታጥቃ ተነስታለች፡፡ የህ ነገር ምንም ቢርበን ብንቸገር ሀገራችን እንዲገባ መፍቀድ አይደለም መታሰቡ
እንኩዋን ፍጹም ኃጢአት ነው፡፡
ጉዳዩን ሊያወግዙ ነው የተባሉት አባቶቻችንም ጭራሽ የስብሰባው ታዳሚዎች
ሆነው ማየት ደግሞ ሌላው አሳፋሪ ታሪካችን ነው፡፡ ˝ሊያወግዙ ነበር ግን የጤና ጥበቃው… አነጋገሩዋቸውና መግለጫውን
ተዉት…˝ ነገሩ ከልብ ከሆነ መግለጫ ለመስጠት ጋዜጠኞችን ቢሮ መጥራት እየተቻለ…… ወይስ ስብሰባው ካለቀ በኋላ
መግለጫውን ይሰጡን ይሆን? ያኔ መቼም እያዘንን መሳቃችን አይቀርም ˝ማሽላ….ይስቃል˝ እንዲሉ አበው፡፡
በዚች ሁለት ቀን ውስጥ ስለ ግብረ ሰዶም በርካታ የፌስ ቡክ ቤተሰቦች ጥቅሶችን ሲያስነብቡን ስለነበር አሁን ጥቅስ አልጠቅስም፡፡ በአጭሩ ግብረ ሰዶም ኃጢአት ነው፡፡ በሁሉም ሃይማኖቶች ኃጢአት ነው፡፡
ታዲያ ለሃይማኖቶች እኩልነት እና መብት ቆሚያለሁ ከሚል አንድ መንግስት
ህዝቦቹ የማይፈልጉትን ነገር ማስገባት ምን የሚሉት ነገር ነው? ወደ ፊትስ ምን ሊያስከትል እንደሚችል የሚያስብ
ከአለቆቻችን አንድ ሰው እንኩዋን እንዴት ይጠፋል ? እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ማህበራዊነት ጎልቶ በሚታይባቸው ህዝቦች
ዘንድ ግብረ ሰዶም በርካታ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡
ከብዙ በጥቂቱ፤
-
አንድነትን ያፈርሳል፤ እኛ ኢትዮጵያውያን አብዛኛው አኗኗራችን በግላዊነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን አንድነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ እንደ ነጮቹ ግለኞች አይደለንም፡፡ በቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ በሌሎች የእምነት ድርጅቶች ዘንድ ተሰብስቦ ማምለክ ነው ልማዳችን፡፡ የሌሎቹን ልተወውና የኛን እምነት ብቻ ብጠቅስ እንኳ፤ የቅዳሴው ስነ ስርአት ወንዶቹን ከሴቶቹ ለይቶ በህብረት ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የወንዶቹና ሴቶቹ መለያት ዋና ምክንያቶች ከሆኑት አንዱ፤ አንዱ ሌላውን እንዳያሰናክል ነው፡፡ አዳር እና ንግሥ በሆነ ጊዜ ታዲያ አይበለውና ይሄ መኣት ከመጣብን የጾታ ምልክት የሌለው ነገር ነውና በመንፈሳዊ አገልግሎታችን እና አንድነታችን ላይ ያለውን አደጋ አስቡት? እግዚአብሔር ሰይጣኑን ይያዝልን፡፡
-
ማህበራዊ ዕሴታችንን ያጠፋል፤ ዕድር ፤ ለቅሶ ፤ ሰርግ የመሳሰሉት ቦታዎች ላይ ይሄ ነገር እየተስፋፋ ከሄደ ምን ሊያስከትል እደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ እግዚአብሔር አያድርግብን!!!
-
ጀግንነታችንን ያጠፋዋል፤ ግብረ ሰዶም ሰይጣናዊ የሆነ ክፉ ተግባር ነው፡፡ ክፉ ነገር ደግሞ በአጭር ጊዜ ነው የሚሰራጨውና ይህ ነገር ሀገር እና ድንበር ወደ ሚጠብቁት ወታደሮቻችን ከተስፋፋ ድንበር ከመጠበቅና ጠላትን ነቅቶ ከመከታተል ይልቅ ሁሉም ራሱን ነው መጠበቅ የሚጀምረው፡፡ ያን ጊዜ ጠላት በቀላሉ የፈለገውን ማድረግ ይችላል፤ ታሪክ ተበላሸ አትሉም ታዲያ? በጦርነት ያልተቻልነው እግዚአብሔርን ይዘን አንድ ላይ ስለሆንን ነው ፡፡ አንድነታችን ደግሞ ከማንም በላይ ያሳፈራቸው አፍሪካን ሁሉ ሊዘርፉ የመጡ ነጮችን ነው፡፡ የተሸነፉበትን አንድነታችንን እና ሃይማኖተኛነታችንን ለማፈራረስ ብቸኛው መፍትሔ ግብረ ሰዶም ነው ያሉ ይመስላል፡፡ ያልመጡበት መንገድ አልነበረም፡፡ መንግስት እነዚሁን አጋንንታዊ ህይወት የሚመሩና ከሞራል ውጭ የሆነ ምግባር የያዙ ጭፍሮችን አበበባ ይዞ(አክብሮ) መቀበሉ ያሳዝናል፡፡
-
መሪዎቻችን የተቀመጡበት ዙፋን እነ አፄ ካሌብ ፣ ቅዱስ ላሊበላ፣ ለማህተብ የሚጨነቁ አፄ ዮሐንስ እና የማርያምን ስም ከጠሩ ያሰቡበት የሚደርሱ ንጉሥ ምኒሊክ ወ.ዘ.ተ.ተቀምጠውበት እንደነበረ እና አጽማቸው ሊወጋቸው እንደሚችል ማሰብ ይኖርባቸዋል፡፡አባቶቻችንም ቢሆኑ ይህንን ነገር አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ፣ አባ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ጴጥሮስን የመሳሰሉ አባቶች ቢኖሩ ይህን ነገር እንኳንስ ዝም ብለው ሊመለከቱ እዲታሰብም እንደማያደርጉ የሚታወቅ ነውና በእነሱ ወንበር ላይ ተቀምጠው አገር ሲበከል ዝም ማለት የለባቸውም፡፡ ˝ወይ ስሜን መልስ ወይ ተዋጋበት˝ እንደሚለው ታሪክ ካልቻሉ በጉልበት ተቀምጦ አገር ማስበከል በነፍስ ብቻ ሳይሆን በታሪክም ያስጠይቃልና ፡ ለሚችል መስጠቱ የተሻለ ነው፡፡ መተማመንን ያጠፋል፤ ይህ ኃጢአት ከተበረታታ ማን ከማን ጋር ይሄዳል? ሠራዊቱም ፣ ተማሪውም ፣ ሰራተኛውም፣ መንገደኛውም ሁሉ የጎሪጥ መተያየት ይጀምራል፡፡ 30 ወንበሮች ብቻ የያዘው ባሳችን(የከተማ አውቶቡስ) እስከ 120 ሰው ይዞ ከቦታ ቦታ ሲጓጓዝ ወሲባዊ ትንኮሳ የሚያጋጥማቸው እህቶቻችን እንዳሉ በተደጋጋሚ ስናነብብ ነበር ፡፡ አሁን የባሰ ሊመጣ ነው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ይያዝልን! እንኳንስ በባስ (አውቶቡስ)ቀርቶ መሸት ሲል ሰዉ ሁሉ እየተፈራራ እንደ ጅብ ጎን ለጎን እንጂ ፊትና ኋላ ላይሄድ ነው ፡፡ የአባቶች አምላክ ለአለቆቻችን ልብ ይስጥልን!!
-
ትውልድን ይቀንሳል፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደምናነበው እና እንደምንሰማው፤ ምንም እንኳ የተለያዩ በሽታዎች እና ረሃብ እያጠቃው ቢሆንም ፣የጥቁር ህዝብ ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ የዘረኞቹ ነጮች አንዱ ስጋት የጥቁር ህዝቦች መብዛት ነው፡፡ ስለዚህ በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ያልተገቡ ርካሽ ህይወትን እንዲመሩ የሚያደርጉት ጥቁሮችን ነው፡ በዜና ማስራጫም ሆነ በኢንተርኔት ስለ ግብረ ሰዶም የሚያሳዩት ብዙውን ጊዜ ጥቁሮች ሲሳሳሙና ጋብቻቸውን ሲፈጽሙ ነው፡፡ ስለዚህ መቼም ቢሆን ለጥቁሮች ነጮች ጥሩ አስበው አያውቁም፡፡ የጥቁርን ዘር ለመቀነስ ስንት ሊረዱን የሚገባ ነገር እያለ ዘር የማይተካበትን እና ከእግዚአብሔር የሚያጣላውን ነውር ይዘውብን መጡ፡፡ የሴቱ ቁጥር ጨምሯል እየተባለ በሚወራበት ጊዜ በቁጥር አነስተኛ እየሆነ የመጣውን ወንድ እርስ በራሱ እንዲጋባ የሚያበረታታ ስብሰባ ከመፍቀድ በላይ ጾታዊ ጥቃት የለም፡፡
በአጠቃላይ ግብረ ሰዶማዊነት ለኢትዮጵያ የሚሰማማት ቀርቶ የሚታሰብላት
አይደለም፡፡ ሀገሪቱ እንድትኖር ከተፈለገ ማለት ነው፡፡ ካለበለዚያ ሁሉም ነገር ስጋት ይሆናል፡፡ እስከዛሬ የሰፈር
ጎረምሶች ስጋት የሴት ልጅ ብቻ ነበር አሁን ግን የወንድም ሊሆን ነው፡፡
ሴት ልጅ ስታመሽና ወንድ ልጅ ደጅ ሲያመሽ የቤተሰብ ስጋት ስለ ሴቷ ብቻ
ነበር ፡፡ ወንድ ከሆነ˝ እሱ ምን ይሆናል? ወንድ ልጅ ነው˝ ይባላል፡፡ አሁን ግን ለወንዱም ስጋት መጣ ለራስዋ
ሳትበላ ልጆችዋን መግባ ጾሟን የምታድር እናት ተጨማሪ ስጋት የሚጨምር ነገር ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ መፍቀድ
በእቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው፡፡
ከዚህ በፊት የሴት ልጅ መደፈር ዜና ነበር ለጆሮዋችን እጅግ ዘግናኝ
የነበረው፡፡ አሁን ወንድ ተደፈረ ሊባል ነው፡፡ የወንድ ደፋሪዎች ስብሰባ ነው የአፍሪካ መዲና የክርስቲያኖች ደሴት
ወይም እንደ መንግስት ˝የመቻቻል አገር˝ የግብረ ሰዶማውያን መሰብሰቢያ ሆነች፡፡ ልማቱ ይሄ ነው እንዴ?
ቅዱስ ጊዮርጊሰ ተዋግቶላት ድልን የተቀዳጀች ፤ ታቦተ ጽዮንን ተቀብላ
በሰላም የኖረችና በሰንበት ማለዳ የቅዳሴ ዜማ የሚንቆረቆርባት ኢትዮጵያ የሰዶማውን መሰብሰቢያ መሆኗ ታሪካዊ ውርደት
ነው፡፡ ስለዚህ ዳግመኛም እንዳይደረግ ከሁለት አካላት መልስ እንሻለን፡፡
-
ከአባቶቻችን፤ ስለዚህ ጉዳይ ለምን ዝም አላችሁ? ይህንን ማስቆም ካልቻላችሁ አባትነታችሁ ምኑ ላይ ነው?
-
ከመንግስት፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ምርጫ 2002 ን ፓርቲያቸው ሙሉ በሙሉ ካሸነፈ በኋላ ከሌሎች አካላት ስለምርጫው በቀረበባቸው አስተያየት ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ˝ይህ ሕዝብ ክብሩን ጠብቆ የሚራብ ሕዝብ ነው˝ ብለው ነበር ፡፡ በእርግጥም ነው ኢትዮጵያዊ ይሞታል እንጂ መልኩን አይቀይርም ክብራችንን ጠብቀን እንሙት!! ሞት ላይቀር እየኖሩ ከመሞት ሞቶ መክበር ይሻላልና:: ያመጡትን ዳቦ ይዘውልን ከነ ርኵሰታቸው የሂዱልን !! መንግስት ለዜጎቹ ሰብእና ከቆመ: መቀሌ ላይ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል እየተከበረ አዲስ አበባ ላይ ያንን ሁሉ ብሔር ብሔረ ሰብ የሚያዋርድ ስብሰባ ለምን ፈቀደ? እርዳታቸው ቀርቶብን ክብራችንን ጠብቀን እንድንራብ ያልተወሰነውስ ለምንድን ነው? መቼም የትኛውም ብሔረ ሰብ የዚህ ደጋፊ አይደለም፡፡
መንግስት ሕዝቡን አዋርዶታል መንፈሳዊና ባህላዊ ማንነታችንን ገደል
የሚከት ነገር አድርጓል በዚህም ምክንያት ሃማኖቱን እና አገሩን የሚያከብር ሁሉ አዝኗል፡፡ በዚህ እግዚአብሔር
ተቆጥቶ የሚያመጣብንን መመለስ የምንችልበት አቅም የለንምና ቁጣውን በትዕግስተ መኣቱን በምህረት እንዲመልስልን
ሁላችንም በያለንበት እናልቅስ፡፡
ወላጆች ለወለዱዋቸው፣ ካህናት ለንስሐ ልጆቻቸው፣ አርቲስቶች (ኪናውያን)
ለሙያ አክባሪዎቻቸው ፤ጸሐፍያን እና ገጣምያን ለአንባቢዎቻቸው ሰባክያን ለምዕመናን ስለዚህ ጉዳይ ሁሉም ወደ
እግዚአብሔር ያለቅስ ዘንድ ያሳስቡ፡፡ ባህታውያን መነኮሳትም ይጸልዩ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር እንዲያርቅልን
ለመሪዎቻችንም ልብ እዲሰጥ፡፡
ካለበለዚያ በእግዚአብሔር ዝናብ የምትኖር ኢትዮጵያ እግዚአብሔር የሰማይ መስኮቶችን ቢዘጋ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ቀላል ነው፡፡ አያድርግብን!! ከቁጣው በፊት ተባብረን ነውርን ካገራችን እናውጣ ፡፡
ኢትዮጵያውን ሆይ እርም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ
ከአገራችሁም አጥፉ ፡፡(ኢያ፤ 6÷18) ጊዜው ከፍቷል ዘመኑም ተበላሽቷል እኛም ተረብሸናል ነገን ፈርተናልና፡፡ ምን
አልባት ነቢዩ ዕንባቆም ከዚህ በታች ያለውን የተናገረበት ዘመን ላይ ደርሰን ይሆን?
የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ ።( ዕን. 3÷7)እግዚአብሔር ከመጣብን ርኵሰት ይጠብቀን አገራችንን ይባርክልን!!! አሜን፡፡
አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን፡፡ እመአምላክ ከዚህ ጭንቅ ነገር ታውጣን !!! አሜን፡፡