መጻሕፍት
በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ መጻህፍት ለንባብ ይቀርብበታል፡፡ መልካም ንባብ ይሆንሎት ዘንድ ከልብ እንመኝሎታለን፡፡
አሁን ያለንበት ዘመን ምን ያህል ፈታኝ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ አለም በስልጣኔ እየሰፋች ስትሄድ የሰዎች ክፋት ደግሞ በተቃራኒ እየባሰና እየከፋ ይሄዳል፡፡እናት ቤተክርስቲያን እያንዳንዱ ሰው ከገበታዋ ያልቆረሰ፡ ያልጠገበ የለም፡፡ መሐይም ሆኖ ሳለ ምሁር ፡ባዶ ሆኖ ሳለ ሙሉ፡ድሃ ሆኖ ሳለ ሐብታም ያድረገች እናት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ በኢትዮጵያውያን ባህል ደግሞ ውለታን መርሳትና መካድ ታላቅ በደል ነው፡፡አሳፋሪም ነው፡፡
አንድን ሰው ከመንገድ ወድቆ የተጣለ ህጻን አግኝቶ ቢያነሳውና ቤቱ ቢወስው፡ አሳድጎ አስተምሮ፡ ለትልቅ ደረጃ አድርሶ፡ ለወግ ለማረግ አብቅቶ በኋላ ግን ይህ ሁሉ የተደረገለት ልጅ አሳዳጊ አባቱን እጅ ሰንዝሮ ቢመታው ይህ አባት ምን ይሰማዋል?
በዘመናችን የምናየው ነገር ቢኖር ይህ ነው፡፡ቤተክርስቲያንን የሚዘርፋት በዛ ፡፡ ግን እኮ የማያልቅ ጸጋ አላትና ዘራፊዎች ያልቃሉ እንጂ ሀብቷ እንደሆነ መቼም አያልቅም፡፡መድኃኒታችን ክርስቶስ “ቤቴስ የጸሎት ቤት ነው፡፡ “ብሎ ገርፎ እንዳስወጣው የሚዘርፉም መውጣታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ግን ስለ ሰው ፍቅር ብሎ የእኛን በደል ታግሶ፡እስከ ሞት ድረስ ለኛ ብሎ ያን ሁሉ መከራ ተቀበለ፡፡ አሁን ደግሞ የታገሰን ሁሉም ነገር በነጻነት ነውና የሰጠን ብትመለሱ ይሻላችኋል ?ወይስ ሰይፌን ብትበላችሁ? ብሎ ምርጫውን ለእኛው ነው የተወው፡፡ ቅዱስ ቃሉ ሲነግረን “እሳትና ውሃ አቅርቤልሃለሁ ወደ ፈለግኸው እጅህን ስደድ “ነው አይደል?
ለመሆኑ ሰው ለምን የዘርፋል?
1.ጊዜያዊ ጥቅም ፈለጋ
ጥቅም የሚለው ቃል ብዙ ትርጉሞች ይኖሩታል ፡፡ ለምሳሌ፦ ስልጣን፡ ስም፡ዝና ወይንም ከበሬታን፡ገንዘብ ወይንም ሐብት ወዘተ፡፡ ስለዚህ ነገር ደግሞ ቅዱስ ቃሉ እንዲይ ይለናል፡፡ በሉቃ 18፡29″እውነት፡እላችኋለሁ፥ስለ እግዚአብሔር፡መንግሥት፡ቤትን፡ወይም፡ወላጆችን፡ወይም፡ወንድሞችን፡ወይም፡ሚስትን፡ወይም፡ልጆችን፡የተወ፤በዚህ፡ዘመን፡ብዙ፡ዕጥፍ፡በሚመጣውም፡ዓለም፡የዘለዓለምን፡ሕይወት፡የማይቀበል፡ማንም፡የለም፡አላቸው።”ይህን ቃል ከዛሬ ስንት ዓመት በፊት ተጽፎልን ይገኛል ፡፡ይህ ቃል ወደ ፊትም ይኖራል፡፡ ጊዜያዊ ገንዘብ ወይንም ሀብት ወይንም ሰም ባጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው ሁሉም የሚያልፉ ናቸው፡፡
2.ባለ ማወቅ
ይህች አለም እንኳን ሰንመለከታት ብዙ ዓይነት እምነቶች ታስተናግዳለች፡፡ታድያ ሁሉም እኮ ትክክለኛ እምነት ይዣለሁ ነው የሚለው፡፡ ከተዋሕዶ ሌላ ትክክለኛና እውነተኛ እንደሌ አሰረግጠው ባለማወቃቸው፡ ይህች ጥልቅ ተምህርት ብዙ፡ተከትሏት ለሚኖሩባት እውነተኛውን መንገድ የምትመራ መሆንዋን ስላልተረዱ ሲጋፏት ሲበድሏት ሲዋጓት ይታያሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዲት እንግዳ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ!! ይህን ይጫኑት—–>ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
3.ሆን ብሎ ለማጥቃት
በዘማናችን ለማልማት ሳይሆን ለማጥፋት፡ ለህይወት ሳይሆን ለሞት ሆን ብለው የተነሱት መናፍቃንና ተሐድሶ ክድሮ ጀምሮ ያጠቁናል ይህ ደግሞ ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነ ው፡፡ እኛም ተኝተን ቤተክርስቲያን መታድግ አቅቶናል፡፡ ከመታድግ ይልቅ በጎሳ ፡በዘር፡ በብሔር መለያየት መርጠናል፡፡
ክርስቶስ ለማን ሲል እንደተሰቀለ ለምን አናስተውለውም! መቼ ነው የምንነቃው? መቼ ነው በመንፈስ የምንጐልምሰው፡(የምንጠነክረው)?
ይህን መጻህፍ ያንብቡ:: ከዚያም የእርሶ ሃላፊነት ምን ያህል ተወጥተዋል? አሁንስ ምን ማድረገ እንዳለቦት የ ሚያሳዮት መጸሐፍ ነው፡፡ነጣቂዎች
መለካም ንባብ ይሁንልዋ!!!!
Source: Teradeani
Subscribe to:
Posts (Atom)