የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ
እርቀ ሰላም
“የቀረወንም ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብደኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው”( ፪ ኛ ቆሮ ፲፩፡፳፰)
ጥቅ /25/2005 ዓ/ም
ቁጥ 083/10/28/2012ለ _______________________________________________________________
ከሁሉ በማስቀደም የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር እንዲሆን እየተመኘን አንዲት ቅድስት ዓለማቀፋዊትና ሐዋርያዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ተከስቶ የማያውቅ በአባቶች መካከል መለያየት ከተፈጠረ ዓመታት ተቆጥረዋል :: ይህ ችግር ለምዕመናን መከፋፈልና አንድነት ማጣት ምክንያት ከመሆኑ ባሻገር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ጥንካሬ ማጣትና ለአገልግሎቱም እንቅፋት መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም ::
If you can’t read the Amharic fonts please read in pdf and click here readpdf
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በአባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት እንዲቻል በአገር ውስጥና ውጪ አገር ከሚገኙ አባቶች እውቅናና ፈቃድ በማግኘት እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ባደረገው ጥረት ከሐምሌ 26-28, 2002 ዓ.ም በአሜሪካ ቨርጅንያ ግዛት ማክሊን ሆቴል ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለቱም ወገኖች የተወከሉ አባቶችን ለማገናኘት ጥረት ማድረጉ ይታዎሳል ::
ሁለተኛውን ጉባኤ ከካቲት 2 ቀን እስከ የካቲት 11ቀን 2004 ዓ/ም በአሜሪካ አሪዚና ከተማ በማካሄድ ከ20 የልዩነት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አባቶች ፊት ለፊት ተገናኝተው ስለቤተ ክርስቲያን ሰላም ተነጋግረው የጋራ መግላጫ ማውጣታቸው ይታወሳል፤ አሁን ደግሞ 3ኛውን ጉባኤ አበው በዳላስ ቴክሳስ ከኅዳር 26-30/2005 ዓ/ም ያካሄዳል፤ ይሁን እንጅ ጉባኤውን ለማካሄድ የገንዘብ እጥረት ስላለብን::
ይህንን ታሪካዊና መንፈሳዊ ጉባኤ ለማዘጋጀት የድርጅትዎ ተሳትፎ እጅጉን አስፈላጊ በመሆኑ የተጀመረው ቤተ ክርስቲያንን አንድ የማድረግ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን በጸሎትና ሐኅሳብ ከሚደረግልን ድጋፍ በተጨማሪ ዝግጅቱ የሚጠይቀው ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ ከዚህ በፊት ስለተደረገልን እገዛ እያመሰገንን የማኅበርዎ አቅም የሚፈቅደውን ያህል የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግልን የሰላምና አንድነት ጉባኤው በአክብሮት ይጠይቃል. ስጦታወትንም ከዚህ በሚከተለው ባንክ ቁጥር ቢልኩልን ይደርሰናል።[Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Council for Peace - Bank Of America MD 99700101 Acct. # 4460193806663]
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ!
መልአከመንክራት ቀሲስ አንዱዓለም ይርዳው አስተባባሪ።